የኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ብፁዕ በካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ የተመራ ለዕብራይስጥ ተናጋሪ ካቶሊኮች የሃዋሪያዊ አገልግሎት 70ኛ ዓመት ክብረ በዓል የኢየሩሳሌም የላቲን ፓትርያርክ ብፁዕ በካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ የተመራ ለዕብራይስጥ ተናጋሪ ካቶሊኮች የሃዋሪያዊ አገልግሎት 70ኛ ዓመት ክብረ በዓል 

በኢየሩሳሌም ለ 70 ዓመታት ያክል ለዕብራይስጥ ቋንቋ ተናጋሪ ካቶሊኮች የሃዋሪያዊ አገልግሎት መሰጠቱ ተነገረ

በእስራኤል ውስጥ የሚገኘው ለዕብራይስጥ ቋንቋ ተናጋሪ ካቶሊካዊያን የተቋቋመው የቅዱስ ያዕቆብ ሃዋሪያዊ አስተዳደር የተመሰረተበትን 70ኛ ዓመት እያከበረ እንደሚገኝ ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ሚያዝያ 24 ቀን 2018 ዓ.ም. በእየሩሳሌም በሚገኘው የኖትርዳም ማዕከል በተከበረው የቅዱስ ያዕቆብ ሃዋሪያዊ አስተዳደር የኢዮቤልዩ ክብረ በዓል ላይ 350 የሚደርሱ ምዕመናን እና ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን፥ የላቲን የኢየሩሳሌም ፓትርያርክ ብፁዕ ካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ በዚህ ዓመታዊው የሃዋሪያው ቅዱስ ያዕቆብ ክብረ በዓል ላይ በተከበረው የኢዩቤልዩ በዓል ወቅት የተካሄደውን መስዋዕተ ቅዳሴ መምራታቸው ተነግሯል።

ቤተ ክርስቲያን በዕብራይስጥ
የቅዱስ ያዕቆብ ሃገረ ስብከት በእስራኤል ውስጥ የቤተክርስቲያን መገኘት ልዩ ምልክት እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፥ ይህች ቤተክርስቲያን በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊነት ላይ ጸንታ የምትገኝ ቢሆንም የዕለት ተዕለት ህይወት የሚገለጽበትን የዕብራይስጥ ቋንቋ እንደምትጠቀም ተገልጿል።

ይህ ክብረ በዓል የሃገረ ስብከቱ ማህበረሰብ ሃዋሪያዊ አስተዳደሩን ለመሰረቱት ካህናት፣ ገዳማዊያት እና ምዕመናን ያላቸውን ምስጋና ለመግለጽ እድል እንደሰጣቸው ተመላክቷል።

የ70ኛ ዓመት ክብረ በዓሉ አከባበር ሁለት ገጽታ የነበረው ሲሆን፥ ዕለቱን አስመልክቶ ከተደረገው የቅዱስ ቁርባን ስግደት ጎን ለጎን ከሰዓት በኋላ በተደረገው መርሃ ግብር የዝማሬ፣ የግል ምስክርነቶች እና በክርስቲያን ሚዲያ ሴንተር የተዘጋጀው ዘጋቢ ፊልም መታየቱ ተገልጿል።

አንድ አካል
እ.አ.አ. ከ 2005 እስከ 2008 ዓ.ም. የቅዱስ ያዕቆብ ሃገረ ስብከት አስተዳዳሪ ሆነው ያገለገሉት ብፁዕ ካርዲናል ፒዛባላ “[የእስራኤልን ሕዝብ] መረዳት” እንዲሁም “ቤተክርስቲያኗን በማገዝ እና ወደፊት እንድትጓዝ በማድረግ ረገድ ማህበረሰቦች ላለባቸው ሃላፊነት እውቅና የመስጠትን አስፈላጊነት አበክረው የገለጹ ሲሆን፥ ይህ ግንኙነት “ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ዛሬ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸው፥ “ሃገረ ስብከቱ ጸንቶ እንዲቆይ ያስቻለው ቤተክርስቲያን የምታወጣው እቅድ ብቻ ሳይሆን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተገነባ መሰረት ስላላት ነው” ብለዋል።

በኢዮቤልዩ ክብረ በዓሉ ወቅት እንደተገለጸው ሃገረ ስብከቱ በየቀኑ በሚባል ደረጃ በመተርጎም፣ አብሮነትን በማሳየት፣ በማዳመጥ እና በማገልገል ተልዕኮውን እያከናወነ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፥ ዓላማውም የተለየች ቤተክርስትያንን መገንባት ሳይሆን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የተመሰረተችውን ቤተክርስትያን ከውስጥ ሆኖ ማገልገል እንደሆነ ተገልጿል።

ከዚህም ባሻገር በችሮታም ሆነ በተግዳሮት ልዩነት ውስጥ ቤተክርስቲያን አንድ አካል እንጂ የደሴቶች ስብስብ አለመሆኗን በአጽንዖት ተገልጿል።

ስጦታ እና ኃላፊነት
ሃገረ ስብከቱ በእስራኤል ውስጥ የሚገኙ የአይሁድ እና የአይሁድ ተወላጅ ያልሆኑ ምዕመናንን፣ ስደተኞችን፣ ሩሲይኛ ቋንቋ ተናጋሪ ቡድኖችን እና የአካባቢው ክርስቲያኖችን ጭምሮ በእስራኤል ውስጥ የሚገኙ የዕብራይስጥ ቋንቋ ተናጋሪ ካቶሊካዊያን ማህበረሰብን አንድ ላይ የሚያሰባስብ ሲሆን፥ ማህበረሰቦቹ በኢየሩሳሌም፣ ቴል አቪቭ–ጃፋ፣ ሃይፋ፣ ቢኤር ሼቫ እና ጢባርያስ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

“ሰባ ዓመት ስጦታ እና በተጨማሪም ኃላፊነት ጭምር ነው” ያሉት እ.አ.አ. ከ 2021 ጀምሮ የቅዱስ ያዕቆብ ሃገረ ስብከት ምክትል አስተዳዳሪ የሆኑት አባ ፒዮትሮ ኤልዛኮ፥ ‘የማህበረሰቡ ተግባር የዘመኑን ምልክቶች ለማዳመጥ፣ የሚቀጥለውን ትውልድ ለመንከባከብ ብሎም የእምነት፣ የውይይት እና የርህራሄ ድልድዮችን ለመገንባት ታማኝ፣ ትጉህ እና ደፋር ሆኖ መቀጠል ነው’ ሲሉ አሳስበዋል።

08 May 2026, 13:28