በኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የጋምቤላ ቫይካሬት ምክትል አስተዳዳሪ ሹመት
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ክቡር አባ ኃይለማርያም መድህን ተስፋይ (የዶንቦስኮ ማሕበር አባል) በኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን፣ የጋምቤላ ቫይካሬት ምክትል አስተዳዳሪ አድርገው መሾማቸው ተገለጸ።
የግል ታሪክ
ክቡር አባ ኃይለማርያም መድህን ተስፋይ (የዶንቦስኮ ማሕበር ካህን) እ.አ.አ ጥቅምት 1 ቀን 1973 ዓ.ም በአሊተና (ኢትዮጵያ) ከአባታቸው አቶ መድህን ተስፋይ እና ከእናታቸው ወ/ሮ አምለሱ ወልደስላሴ ተወለዱ። በጎተራ (አዲስ አበባ) በሚገኘው የሳሌዚያን ማኅበር የቅዱስ ዮሐንስ ቦስኮ ገዳም ውስጥ ቆይታ አድርገው ካበቁ በኋላ በማሕበራቸው፣ በቤተክርስቲያን የመተዳደሪያ ደንብ እና ቀኖና መሰረት መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ለመምራት የምያስችላቸውን ቋሚ ማሐላ እ.አ.አ በ2001 ዓ.ም በአዲስ አበባ አድርገዋል። እ.አ.አ በግንቦት 4 ቀን 2003 ዓ.ም በአዲግራት ማዕረገ ክህነት ተቀብለዋል።
የሚከተሉትን የስራ መደቦች እና ተጨማሪ ጥናቶችን አጠናቅቋል፡- ቄሰ ገበዝ፣ ቆመስ እና ገንዘብ ያዢ ሆነው በአድዋ (እ.አ.አ 2003-2006) አገልግለዋል። በሮም ከሚገኘው የጳጳሳዊ ሳሌዥያን ዩኒቨርሲቲ በሥነ-መለኮት ትምህርት የማስትሬት ዲግሪ አጠናቋል (እ.አ.አ 2006-2009)፣ የቲዎሎጂ (ነገረ-መልኮት) ትምህርት ፕሮፌሰር ሆነው በኡቱሜ (ኬንያ) (እ.አ.አ 2009-2013) አገልግለዋል፣ የዶክትሬት ዲግሪ በቲዎሎጂ (ነገረ-መልኮት) ትምህርት ከሮማ ጳጳሳዊ ሳሌዥያን ዩኒቨርሲቲ (እ.አ.አ 2013-2016) አጠናቀዋል፣ በአዲስ አበባ የመካኒሳ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን (አዲስ አበባ) ቆመስ እና ዳይሬክተር ሆነው (እ.አ.አ 2016-2019) አገልግለዋል፣ ኢትዮጵያ- ኤርትራ "ኪዳነ ምሕረት" የሣሌዥያ ማሕበር አለቃ ሆነው (እ.አ.አ 2019-2025 ዓ.ም) አገልግለዋል፣ በኢትዮጲያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ገዳማት/ገዳማዊያን የበላይ አለቆች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው (እ.አ.አ 2020-2025) አገልግለዋል።
መልካም የአገልግሎት ዘመን ይሆንሎት ዘንድ የቫቲካን ዜና ክልብ ይመኛል፣ እግዚአብሔር ጥሪዎን ይባርክ!