ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም 'አርተፊሻል ኢንተለጀንስ' ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም 'አርተፊሻል ኢንተለጀንስ'   (REUTERS)

በሰሜናዊ ታይላንድ የምትገኘው ቤተክርስቲያን በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘመን ስነ ምግባር ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ አሳሰበች

የዲጂታል ቴክኖሎጂዎች እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወይም ሰው ሰራሽ አስተውሎት ህብረተሰቡን ወደራሳቸው ጎራ በመቅረጽ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን፥ በሰሜናዊ ታይላንድ የሚገኙ የቤተክርስትያን መሪዎች በዚህ ዘመን በህሊና፣ እሴቶች እና ስነ-ምግባራዊ ሃላፊነት ላይ ጠንካራ መሰረት ሊኖር እንደሚገባ አበክረው ገልጸዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በተያዘው የጎረጎሳዊያኑ ዓመት መጀመሪያ ላይ በሰሜናዊ ታይላንድ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የ 2026 ዓመታዊ ክልላዊ ጉባኤ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ምስራቅ ከላኦስ ጋር በሚዋሰነው ናኮን ፋኖም ግዛት ውስጥ መካሄዱ የተነገረ ሲሆን፥ በዚህ ጉባኤ ላይ ወደ 200 የሚጠጉ ካህናት፣ አምስት ብፁዓን ጳጳሳት እና በርካታ የላኦስ ልዑካን መሳተፋቸው ተነግሯል።

ካህናትን ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር እንዲላመዱ ማሰልጠን 
ጉባኤው ያተኮረው የቅድስት መንበር የእምነት አስተምህሮ፣ የባህል እና የትምህርት ጽህፈት ቤት በቅርቡ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና በሰዎች እውቀት መካከል ስላለው ግንኙነት አስመልክታ ‘አንቲኳ ኤት ኖቫ’ በሚል ርዕስ በወጣው የቫቲካን ሰነድ ላይ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን፥ በጉባኤው ላይ በዋናነት ንግግር ካደረጉት ሰዎች መካከል የታይላንድ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ የማህበራዊ ግንኙነት ፅህፈት ቤት ዋና ፀሀፊ የሆኑት አባ ጆሴፍ አኑቻ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በተመለከተ ቤተክርስቲያን ያላትን ግንዛቤ አስመልክተው ለካህናት እና ለሃዋሪያዊ አገልግሎት ሰራተኞች ንግግር ማድረጋቸው ተገልጿል።

አዳዲስ የዲጂታል መሳሪያዎች
አባ ጆሴፍ ባደረጉት ንግግር በሰው ሰራሽ አስተውሎት ተፈጥሮ እና ውስንነት ላይ በማተኮር ‘ሰው ሰራሽ አስተውሎት እውነተኛ እውቀት፣ ንቃተ-ህሊና ወይም ግንዛቤ እንደሌለው’ ጠቁመው፥ ከዚህም በተጨማሪ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም ‘አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ’ ሕሊና እና ሕይወት የለውም በማለት አክለዋል።

‘አንቲኳ ኤት ኖቫ’ በተሰኘው የቫቲካን ሰነድ ላይ በመመስረት አስተያየታቸውን የሰጡት ካህኑ፥ ሰነዱ እምነትን ለማስተላለፍ አደራ ለተሰጣቸው በተለይም በዲጂታል አካባቢዎች ለሚሰሩ ካህናት እና አገልጋዮች ‘የስነ ምግባር ጠቋሚ’ መሳሪያ እንደሆነ ጠቅሰው፥ ‘ቴክኖሎጂ የሰውን ልጅ ለማገልገል የተፈጠረ እንጂ አልጎሪዝም ታሪካችንን እንዲጽፍ መፍቀድ ዬለብንም’ በማለት ተሳታፊዎችን ማሳሰባቸው ተነግሯል።

አባ ጆሴፍ በተጨማሪም “በመረጃ እና በጥበብ” መካከል ያለውን ውጥረት በማስታወስ፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት በሚያገኘው መረጃ ላይ በመመስረት “የመተንተን እና የመተንበይ” አቅሙ የላቀ ቢሆንም፥ የሰው ልጅ ፍቅር፣ ነፃነት እና የማሰብ ችሎታ “የማይገመት እና የተቀደሰ” ሆነው እንደሚቀጥሉ በአጽንዖት ተናግረዋል።

እውነት ሐሰተኛ መረጃን እና አሉባልታዎችን ያጣራል
አባ ጆሴፍ ይበልጥ አሳሳቢ የሆኑ ጉዳዮችን በማስታወስ በዲጂታል ዓለም ውስጥ በጉልህ ስለሚታየው ስለ ሃሰተኛ መረጃ ጉዳይ ያነሱ ሲሆን፥ ከተሳሳተ መረጃ ባሻገር የህዝብ ንግግርን የሚያዛቡ እና አመለካከቶችን የሚቀይሩት ሃሰተኛ ወሬዎች እና አሉባልታዎች የሚያሳድሩት ተጽእኖ እየተስፋፋ መምጣቱን አስጠንቅቀዋል።

“የሃሰተኛ መረጃ አደጋ በተለይ ሌሎችን ለማጥቃት ወይም ለመጉዳት ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ በግልጽ ይታያል” የሚለውን የቫቲካን ሰነድ፥ ምስሎቹ ወይም ቪዲዮዎች ራሳቸው የሰው ሠራሽ አስተውሎት ሥራዎች ሊሆኑ ቢችሉም የሚያደርሱት ጉዳት ግን ከባድ እንደሆነ በመጥቀስ፥ ይህም ‘በሰለባዎቹ ልብ ውስጥ ጥልቅ ጠባሳ’ እና ‘በሰብዓዊ ክብራቸው ላይ እውነተኛ ቁስሎችን’ እንደሚተው አብራርቷል።

አባ ጆሴፍ የፈጠራ ይዘትን ከትክክለኛ መረጃ መለየት አስቸጋሪ እየሆነ መምጣቱን አስጠንቅቀው፥ ለእውነተኛ ውይይት እና የእምነት ልምምድ አስፈላጊ የሆኑት የመተማመን መሠረቶች ናቸው ብለዋል።

ኃላፊነት የተሞላበት የ ኤአይ አጠቃቀም
አባ ጆሴፍ የሃይማኖት አባቶች እና የቤተክርስቲያን ተቋማት በግልፅነት፣ በማካተት እና በተጠያቂነት መርሆዎች እንዲመሩ በማበረታታት፥ በኤአይ ሥነ ምግባር ላይ በሚደረጉ ዓለም አቀፍ ውይይቶች ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመው ለእነዚህ ተግዳሮቶች ምላሽ ይሆናሉ ያሏቸውን ሃሳቦች አካፍለዋል።

አንቲኳ ኤት ኖቫ የተሰኘው የቫቲካን ሰነድ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ቴክኖሎጂ ከሚያመጣው የአቅም እድገት ጋር በተመጣጠነ መልኩ ሰብዓዊ ሃላፊነት፣ እሴቶች እና ህሊና አብሮ ማደግ እንደሚገባ ከሚገልጸው አስተምህሮታቸው ጋር እንደሚስማማ ያስታወሱት አባ ጆሴፍ፥ እነዚህ መርሆች የሃዋሪያዊ አገልግሎት አሠራርን፣ የዲጂታል ወንጌላውያንን እና ተቋማዊ ውሳኔዎችን ማሳወቅ አለባቸው ብለዋል።

ግልጽነት
አባ ጆሴፍ ግልጽነት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አሰራር ውስጥ፣ በተለይም ከፍተኛ ማህበራዊ ተፅእኖ ባላቸው አካባቢዎች ላይ ሊኖር እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው የገለጹ ሲሆን፥ ግልጽነት የተደበቀውን ነገር ለማሳየት የሚደረገውን ጥረት፣ የተሰወረ እና ብዙውን ጊዜ የኤአይ ስርዓቶች ውሳኔዎችን እና ምክሮችን የሚያመነጩበት ግልጽነት የሌላቸው ሂደቶችን ለማሳየት ያለውን ጠቀሜታ ገልጸዋል።

ይህ በተለይ በትምህርት፣ በአስተዳደር፣ በኮሚዩኒኬሽን እና በማህበራዊ አገልግሎቶች በመሳሰሉት ‘ከፍተኛ ተፅእኖ በሚፈጠርባቸው አካባቢዎች’ የቴክኖሎጂ ማጭበርበር ከባድ መዘዝ ሊያስከትል እንደሚችል አስረድተዋል።

ቴክኖሎጂ የሰው ልጅን እና የቤተክርስቲያኗን ተልዕኮ በትክክል የሚያገለግለው በግልጽነት፣ ስነ ምግባርን በመቆጣጠር እና በሰዎች ማስተዋል ብቻ እንደሆነ የጠቆሙት ካህኑ፥ በእነዚህ ክልላዊ ጉባኤዎች በመሳሰሉ ተነሳሽነቶች በሰሜናዊ ታይላንድ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ወሳኝ፣ እምነትን መሰረት ካደረገ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር መተሳሰርን፣ በዲጂታል ዘመን በሃላፊነት፣ በጥበብ እና በወንጌል ታማኝነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ማስፋፋቷን ቀጥላለች በማለት አጠቃለዋል።

13 Feb 2026, 11:49