ፈልግ

 እ.አ.አ. በ 2023 በፖርቱጋል በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ቀን የደቡብ ኮሪያ ወጣቶች ሴኡል የ 2027 የዓለም ወጣቶች ቀንን እንደምታዘጋጅ በተነገረበት ወቅት ደስታቸውን ሲገልጹ  እ.አ.አ. በ 2023 በፖርቱጋል በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ቀን የደቡብ ኮሪያ ወጣቶች ሴኡል የ 2027 የዓለም ወጣቶች ቀንን እንደምታዘጋጅ በተነገረበት ወቅት ደስታቸውን ሲገልጹ   (AFP or licensors)

የሴኡል ሃገረ ስብከት የዓለም ወጣቶች ቀን ዓርማዎችን የሚገልጽ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄድ መንፈሳዊ ንግደት ማስጀመሩ ተነገረ

የሴኡል ሃገረ ስብከት የዓለም ወጣቶች ቀንን (WYD) አስመልክቶ የሚካሄዱ በሃገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄዱ መንፈሳዊ ንግደት ምልክቶችን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ በዚህ በመዮንግዶንግ ካቴድራል በተካሄደው ሥነ ስርዓት እንደ አርማ የሚያገለግሉ 15 የሚሆኑ ቅርፃ ቅርፆችን በመባረክ ይፋ መደረጉ ተገልጿል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

እነዚህ 15 ቅርፃ ቅርፆች በኮሪያ የሚገኙ እያንዳንዱን ሀገረ ስብከት የሚወክሉ እና የሃገረ ስብከቶቹ ስሞች የተፃፉበት ሲሆን፥ ከዚህም በተጨማሪ እ.አ.አ. በ 2027 በሴኡል የሚካሄደውን የዓለም የወጣቶች ቀንን አስመልክቶ የሚደረጉ የሀገር ውስጥ መንፈሳዊ ንግደቶች መጀመሩን የሚያመላክት መሆኑ ተነግሯል።

የዓለም የወጣቶች ቀን መስቀል እና ‘ሳሉስ ፖፑሊ ሮማኒ’ የተሰኘው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ምስል በጎረጎሳዊያኑ 2025 ዓ.ም. በመላው ዓለም አቀፍ የመንፈሳዊ ንግደት መርሃ ግብሮች ላይ የወጣቶች ጸሎት እና ተስፋ ይዘው ሮምን ጨምሮ በዘጠኝ ሀገራት በወጣቶች ኢዮቤልዩ ወቅት ተጉዘው እንደነበር ይታወቃል።

ሊቀ ጳጳስ ፒተር ሶን-ታክ ቹንግ ጥር 20 የተካሄደውን ይሄንን የቡራኬ ሥነ ስርዓቱን የመሩ ሲሆን፥ ብፁዕነታቸው ለዓለም ወጣቶች ቀን ዝግጅቱ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት እነዚህ ቅርፃ ቅርፆች የጋራ ተልዕኮ እና ፀጋን እንደሚያስታዉሱ በመግለጽ፥ ‘በየሀገረ ስብከቱ ስም የተሰየሙት እነዚህ ቅርፃ ቅርፆች በዚህ ዝግጅት ላይ ለመካፈል የሚዘጋጁትን ሁሉ ጥሪያቸውንና ያገኙትን ጸጋ ያስታውሳል’ ብለዋል።

ሊቀ ጳጳስ ቹንግ ምዕመናን “በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወጣቶችን ሞቅ ባለ መንፈስ በሚቀበለው የወጣቶች በዓል” ለሚደረገው ዝግጅት ራሳቸውን ሙሉ በሙሉ እንዲሰጡ አሳስበው፥ ቅርፃ ቅርፆቹን የሚያዩ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመምሰል እንዲያድጉ ጸልየዋል።

ሊቀ ጳጳሱ የዓለም ወጣቶች ቀን ለሥነ-ምህዳር ኃላፊነት የሚሰጠውን ትኩረት በማንፀባረቅ፥ ቅርፃ ቅርፆቹ የተሠሩት ከጧፍ እና ሙሉ በሙሉ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል ከሚችል ወረቀት እንደሆነ አብራርተዋል።

የቅርፃ ቅርፆቹ ዲዛይን የተሰራው በጎ ፈቃደኛ በሆነው ወጣት ጁንግ-ሁን ቾ ሲሆን፥ መጠኑ እንደየሀገረ ስብከቱ ትንሽ ቢለያይም፥ እያንዳንዱ ቅርፅ 1,500 ሚሊ ሜትር ስፋት እና 800 ሚሊ ሜትር ቁመት እንዳለው ተገልጿል።

አስራ አምስቱም ቅርፃ ቅርፆች በአገር አቀፍ ደረጃ ለሀገረ ስብከቶች የሚከፋፈሉ ሲሆን፥ በሀገረ ስብከቱ እና በቁምስና ደረጃ በሚካሄዱ ዝግጅቶች ላይ በኮሪያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የአንድነትና የኅብረት ምልክት ሆነው ያገለግላሉ ተብሏል።

‘የዓለም ወጣቶች ቀን መስቀል እና የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ምስል’ የሚል ስያሜ የተሰጠው እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው መንፈሳዊ ንግደት ጥር 13 በወንጁ ሀገረ ስብከት የተጀመረ ሲሆን፥ ዓርማዎቹ ምልክቶቹ ሰኔ 2019 ዓ.ም. ወደ ሴኡል ሃገረስብከት ከመመለሳቸው በፊት በአስራ አምስቱም ሀገረ ስብከቶች እንደሚዞሩ ተገልጿል።

22 Jan 2026, 14:52