በዓለም ዙሪያ የሚሰደዱ ክርስቲያኖች ቁጥር ወደ 388 ሚሊዮን ከፍ ማለቱ ተገለጸ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በዓለም ዙሪያ ለስደት እና ለዓመፅ የተጋለጡ ክርስቲያኖች ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ8 ሚሊዮን ሰዎች ጨምሯል፣ ይህም በቁጥር አሃዝ ሲሰላ 388 ሚሊዮን መድረሱ ተዘግቧል።
"እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ይህ እንደገና ከመቼው ጊዜ የበለጠ ከፍተኛ የሆነ ቁጥር የተመዘገበበት ዓመት ነው" ሲሉ የ"Open Door" አለም አቀፍ ድርጅት ዳይሬክተር ክርስቲያን ናኒ ጥር 06/2018 ረቡዕ ዕለት በዓለም ዙሪያ ስለሚሰደዱ ክርስቲያኖች እ.አ.አ የ2026 የዓለም የክትትል ዝርዝርን ይፋ የሆነበትን ሪፖርት ይፋ አድርገዋል። "ከእነዚህ 388 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ 201 ሚሊዮን የሚሆኑት ሴቶች ወይም ልጃገረዶች ናቸው፤ 110 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው" ሲሉ ከቫቲካን ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
ዓመፅ እና መድልዎ
በዓለም የክትትል ዝርዝር ሪፖርት መሠረት፣ “ጽንፈኛ” ተብሎ ሊገለጽ የሚችል ፀረ-ክርስትና ስደት ያለባቸው አገሮች ቁጥር ከ13 ወደ 15 ከፍ ብሏል። ሰሜን ኮሪያ ክርስቲያን መሆን በጣም አደገኛ የሆነባት አገር ሆና ቀጥላለች። አስደንጋጭ የስደት ደረጃ ያላቸው አገሮች ዝርዝር ሶማሊያ፣ ኤርትራ፣ ሊቢያ፣ አፍጋኒስታን፣ የመን፣ ሱዳን፣ ማሊ፣ ናይጄሪያ፣ ፓኪስታን፣ ኢራን፣ ህንድ፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ምያንማር እና ሶሪያንም ያካትታል። በክትትል ዝርዝር ሪፖርት መሠረት ሶሪያ ከ “ከፍተኛ” ወደ “ጽንፈኛ” ደረጃ ተሸጋግራለች።
የ"Open Door" አለም አቀፍ ድርጅት ዋና ዳይርክቴር የሆኑት ክርስቲያን ናኒ ለቫቲካን ኒውስ እንደተናገሩት፣ አዲሱ የፖለቲካ ኃይል አሁንም በከፊል “የተበታተነ” በመሆኑ በሶሪያ ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖች አሁንም አደጋ ላይ ናቸው ብለዋል፣ ይህም በቅርብ ቀናት በአሌፖ በተከሰቱት ግጭቶችም ታይቷል ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
“በመረጃችን መሠረት፣ በሶሪያ የቀሩት 300,000 ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው - ማለትም ከአስር ዓመታት በፊት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያቲያኖች በሶሪያ ይኖሩ ነበር” ብለዋል።
ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ አገሮች ላይ ትኩረት ይደረግ
ከዚህ ቀደም ከሰሃራ በታች ባሉ አገሮች ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ ይፈጸም የነበረው ጥቃት እና ስደት ከቀነሰ በኋላ፣ የክርስቲያኖች ግድያ ቁጥር እንደገና ጨምሯል፣ በቀን ከ4,476 ወደ 4,849 - በየቀኑ ጭማሬ አሳይቷል። ናይጄሪያ የዓመፅ ማዕከል መሆኗ ተረጋግጧል፤ 3,490 ተጎጂዎች ተገድለዋል።
በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩት ክርስቲያኖች ቁጥር ከሞላ ጎደል አልተለወጠም (እ.አ.አ በ2024፣ ከ4,744 ጋር ሲነጻጸር 4,712 ደርሷል)፣ የታገቱ ክርስቲያኖች ቁጥር ደግሞ ቀንሷል (እ.አ.አ በ2024፣ ከ3,775 ጋር ሲነጻጸር ወደ 3,302 ቅናሽ አሳይቷል)።
በቤተክርስቲያናት ላይ የሚሰነዘሩት ጥቃቶችም ቀንሰዋል (ከ7,679 ወደ 3,632)፣ እንዲሁም በቤቶች ወይም በሱቆች ላይ የሚሰነዘሩት ጥቃቶች (ከ28,368 ወደ 25,794 ቅናሽ አሳይተዋል)፣ የጥቃት፣ የአስገድዶ መድፈር እና የግዳጅ ጋብቻ ሰለባዎች ቁጥር ጨምሯል (ከ3,944 ወደ 5,202)።
የ"Open Doors" አለም አቀፍ ድርጅት ዳይሬክተር ክርስቲያን ናኒ እንደ ተናገሩት ከሆነ ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ አገራት እ.አ.አ በ2026 ዓ.ም የክትትል ዝርዝር ውስጥ "ልዩ የምልከታ" ሥፍራ አድርገው አስፍረዋል፣ በተለይም ክርስቲያኖችን ለዓመፅ የሚያጋልጡ "ደካማ መንግስታት" በመኖራቸው የተነሳ ከፍተኛ ስደት እየተከሰተ መሆኑም ተገልጿል።
“የክርስትና የስበት ማዕከል ወደ አፍሪካ ተሸጋግሯል፣ ነገር ግን በዋናነት ጥቃት የሚሰነዘረው እዚያ ነው” ሲሉ የ"Open Doors" አለም አቀፍ ድርጅት ዳይሬክተር ክርስቲያን ናኒ አክለው የገለጹ ሲሆን፣ አፍሪካ ከዓለም አንድ ስምንተኛ የሚሆነው የክርስቲያን ሕዝብ የሚኖርበት አህጉር እንደሆነም አክለው ገልጸዋል።
ሱዳን በተለይ ወሳኝ ከሆኑ አገሮች አንዷ መሆኗን አክለው የገለጹት ዳይሬክተሩ፣ በእርስ በርስ ጦርነት ምክንያት አሁን በከፍተኛ ደረጃ ክርስቲያኖች የሚሰደዱባት አገር ሆናለች፣ እንዲሁም ናይጄሪያ፣ ማሊ፣ ኒጀር፣ ቡርኪና ፋሶ፣ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ እና ሞዛምቢክ በክርስቲያኖች ላይ ስደት የሚፈጸሙባቸው ስፍራዎች እንደሆኑም ተገልጿል።
በእነዚህ ደካማ ሁኔታዎች ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች ከሃይማኖታዊ ገጽታ ጋር የሚጣመሩባቸው የተለያዩ ምክንያቶች አሏቸው።
በናይጄሪያ የተፈጸሙ ጥቃቶች
የ"Open Doors" አለም አቀፍ ድርጅት እ.አ.አ የ2026 ዓ.ም የክትትል ዝርዝር ሪፖርት ረቡዕ ዕለት ጥር 06/2018 ዓ.ም በሮም በሚገኘው የጣሊያን የሕግ መወሰኛ ፍርድ ቤት አዳራሽ ውስጥ ይፋ የሆነ ሲሆን
ይህ እ.አ.አ የ2026 ዓ.ም የክትትል ዝርዝር ሪፖርት ከናይጄሪያ የመጣ የዐይን ምስክር ዘገባ ጋር አብሮ ቀርቧል፣ ይህም እየጨመረ በመጣው አለመረጋጋት በጣም ከተጎዱት አገሮች አንዷ ናይጄሪያ መሆኗን ያሳያል።
በቅርብ ቀናት፣ የ"Open Doors" አለም አቀፍ ድርጅት እ.አ.አ የ2026 ዓ.ም የክትትል ዝርዝር ሪፖርት አሜሪካ የገና በዓል ሰሞን በናይጄሪያ በጽንፈኞች ላይ ከሰነዘረችው ጥቃት በኋላ በሽብር ቡድኖች ሊወሰዱ ስለሚችሉ የበቀል እርምጃዎች ከተጨነቁ ክርስቲያኖች በርካታ አስተያየቶችን ሰብስቧል፣ እንዲሁም በሰሜን ናይጄሪያ የተከሰቱትን የቅርብ ጊዜ የዓመፅ ክስተቶች ዘግቧል።
እነዚህም እ.አ.አ ታህሳስ 29/2025 ዓ.ም በአዳማዋ ግዛት በምዕራብ አፍሪካ ግዛት የእስላማዊ መንግሥት ግዛት (ISWAP) በተሰነዘረባቸው ጥቃቶች 14 ሰዎች ሰለባዎች እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን እንዲሁም እ.አ.አ ጥር 4 ቀን 2026 ዓ.ም በኒጀር ግዛት በዴማ በሚገኝ የገበያ ቦታ ላይ ጥቃት የፈጸሙት ማንነታቸው ያልታወቁ የታጠቁ ሰዎች እጅ የደረሱ በርካታ ጥቃቶች ብዙ ሰዎች ሰለባዎች እንዲሆኑ ማድረጉ ይታወሳል።