በምሥራቅ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ዘንድ የነነዌ ጾም ተከበረ
በያዝነው ሳምንት ከምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት የወጣው ዜና በተለይም በአብያተ ክርስቲያናቱ ዘንድ የነነዌ ጾም በጥልቅ መከበሩን አስታውቋል።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
በያዝነው ሳምንት የምሥራቅ ክርስቲያን ማኅበረሰቦች በአሦራውያን ባሕል ውስጥ ሥር የሰደደውን እና ከዐቢይ ጾም በፊት የሚከበረውን የሦስት ቀናት የነነዌ ጾም ማድረጋቸው ታውቋል።
ጾሙ ዮናስ በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ያሳለፈውን ሦስት ቀናት የሚያስታውስ እና እንዲሁም የነነዌ ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያውን ከሰሙ በኋላ ንስሐ የገቡበትን ሁኔታ የሚያስታውስ እንደ ሆነ ታውቋል። “Watch the video”
የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ዮናስ ሕዝቡ ከተሳሳተበት መንገድ ተመልሶ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንዲመለስ ለመጥራት ወደ ነነዌ መላኩን ይገልጻል። የነነዌ ነዋሪዎች ለመለኮታዊ ቅጣት ሲጋለጡ ጾም እና ጸሎት ማድረግን እንደሚመርጡ ሲታወቅ ይህም በእግዚአብሔር ምሕረት የጋራ መለወጥን ለማግኘት የሚያደርጉት ተግባር እንደሆነ ታውቋል።
የነነዌ ጾም ዛሬም ቢሆን በአብዛኛዎቹ የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ የሚከበር ሲሆን፥ የመንጻት፣ የጸሎት እና የአንድነት ጊዜ ሆኖ በጥንታዊው የምሥራቅ አብያተ ክርስቲያናት ባሕል ሕያው ሆኖ መቀጠሉ ታውቋል።
31 Jan 2026, 16:27