ፈልግ

የባይካል ሐይቅ የባይካል ሐይቅ 

ኢኮኖሚውን እንደገና በማስጀመር ላይ የሚወያይ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተዘጋጀ

“ኢኮኖሚውን እንደገና ማስጀመር” በሚል ርዕሥ በካስቴል ጋንዶልፎ ከተማ ከህዳር 19-21/2018 ዓ. ም. ድረስ ዓለም አቀፍ ስብሰባ እንደሚካሄድ ታውቋል። በ “ፍራንችስኮስ ኢኮኖሚ” አስተባባሪነት የሚዘጋጀው ይህ ዓለም አቀፍ ስብሰባ፥ ኢኮኖሚን በኢዮቤልዩ አንፃር እንደገና ለማጤን፣ በማህበራዊ ፍትህ፣ በምድራችን እንክብካቤ እና ከዕዳ ነፃ መሆን ላይ ያለመ እንደሆነ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ውስጥ ከዘፍ. 1 ጀምሮ እንደተጠቀሰው እረፍት ብዙውን ጊዜ ወደ መዳን እና ወደ ሕይወት እርካታ የሚደረግ ጉዞ፣ እንደገና በመታደስ ሰላምን ማግኘት የምንችልበት ቦታ እንደሆነ ይገለጻል። እረፍት ቦታ ከሆነ በዚህች ምድር ላይ የት ማግኘት እንደምንችል ራሳችንን ልንጠይቅ እንችላለን። ምድር እራሷን እና እኛን እንደገና እንድታድስ እንፈቅዳለን? “ያ አምሳኛው ዓመት ለእናንተ ኢዮቤልዩ ይሆናል፤ በእርሱም አትዝሩ፥የምታበቅለን አትጨዱ፥ የወይኑንም ፍሬ አታከማቹ” (ዘሌ. 25:11)።

መስዋዕትነትን በመክፈል የአንድ ሰው መሬት ሳይታረስ የማቆየት ጥያቄ በፍጹም የሚቻል አይመስልም። እግዚአብሔር በፍጥረት ላይ ያለንን አመለካከት ይለውጣል፣ በዚህም ምክንያት እኛ የዚህ አካል መሆናችንን እና በዚህም ምክንያት ለምድር እና ለፍጥረታቷ በሙሉ ኃላፊነት እንዳለብን ያሳየናል።

የኢዮቤልዩ በዓል “ቤታችንን፣ ሃብታችንን እና ኢኮኖሚያችንን ለማስተዳደር ያለንን አካሄድ እንደገና ለማጤን ዕድል ይሰጠናል። ይህ ከማኅበረሰባችን የኢኮኖሚ ህጎች እና የአኗኗር ዘይቤዎች ጋር የሚጋጭ ቢሆንም በመጀመሪያ ደረጃ ምድርን እንደ ትውልድ፣ ተስፋ እና ትርጉም ቦታ እንደ ሆነች ወደ መገንዘብ የሚያደርስ እርምጃ መሆኑን ያሳያል።

ምድር ያለ ቅድመ ሁኔታ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ሃብት ወይም በአገልግሎት ላይ ያለ ነገር አይደለም፣ ይልቁንም ከጎናችን የሚመገብና የሚለወጥ ሕያው አካል ናት። ይህ ግንዛቤ ኢኮኖሚውን የምንይዝበትን መንገድ እንዴት ሊለውጠው ይችላል? የዕረፍትን ጽንሰ-ሀሳብ በኢኮኖሚያዊ እና ሥነ-ምህዳራዊ ዘርፎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እና የግል ተግባሮቻችንን እና የጋራ ጥረቶቻችንን እንዲመራ ልንፈቅድለት እንችላለን።

አፈርን፣ ውሃን እና አየርን እንደገና ማደስ

ዕረፍትን በሰውነታችን ውስጥ የሕዋስ ዳግም መወለድን የሚያበረታታ ዘዴ አድርገን እንደምናስብ ሁሉ ምድርም እንዲሁ እንድታደርግ መፍቀድ አለብን። ይህ እንደ መሬት ቆፍሮ መተው፣ የሰብል ሽክርክሪት እና የዕረፍት ሜዳዎችን ያሉ ባህላዊ ልምዶችን ማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን ነገሮችን የምናለማበት እና የምናመርትበትን መንገድ እንደገና ማጤንንም ያካትታል። በመፈክር ጀርባ ከመደበቅ ይልቅ ሰብሎችን ለማባዛት፣ ብክለትን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ እና የተፈጥሮ ሃብቶችን ከማሟጠጥ ይልቅ የሚሞሉ የምርት ዑደቶችን ግምት ውስጥ ማስገባት አለብን። የከተማ አፈርን ለማዳረስ ወይም ዘላቂ የመጓጓዣ አውታረ-መረቦችን ለማስተዋወቅ በሚደረጉ የመልሶ ማቋቋም የግብርና ልምዶችን በመጀመር ነገሮችን በተለየ መንገድ ማድረግን በመማር ምድር እንደገና እንድትታደስ መፍቀድ አለብን።

የምርት ፍጥነት ማርገብ እና ፍጆታን መቀነስ

በቆሻሻ የተበከለ የተፈጥሮ ገጽታ የሰው ልጅ የመፍጠር ችሎታ ታላቅ ስጦታን ያጣ መሆኑን ያመለክታል። ማረፍ ማለት ምርትን ማዘግየት እና ውድ ሀብቶችን የሚጠቀሙ እና ወደ ቆሻሻ የሚቀይሩ ነገሮች ፍጆታ መቀነስ ማለት ነው። ይህም ምድርን የሚያረክሰው እና ለሁሉም ፍጥረታት የማይመች ያደርጋታል። ቅድስናዋን እና ንጽህናዋን ይጥሳል። በማኅበረሰባችን ውስጥ እንደ አዲስ ደንብ የንግድ ማሽቆልቆልን እና ዕቃዎችን ለመጋራት ያለንን ቦታ እንመልከት።

ኃይልን እንደገና መሙላት

ምድር ብዙ ነገሮችን ትሰጠናለች። ነገር ግን ብዙ ጊዜ ይህንን ሃብት መቀበል እና መንከባከብ ይሳነናል። እንደ ቅሪተ አካል ነዳጆች ወይም ውሃ ያሉ ታዳሽ ያልሆኑ ሃብቶችን እንዴት እንደምንጠቀም በማሰብ የኃይል ፍላጎታችንን በተለየ መንገድ መለካት እንችላለን። በንጹህ ልብ ተነሳስተን፥ ለምሳሌ ሃብትን የሚጠይቁ ቴክኖሎጂዎችን እንዴት እንደምንጠቀም ትኩረት በመስጠት አላስፈላጊ ፍጆታን መቀነስ እንችላለን። እንዲሁም የሚገኘውን ኃይል ሳያባክኑ በማከማቸት ምድርን ለመሙላት አዳዲስ መንገዶችን መፍጠር እንችላለን። ይህን ሃብት ያለ ምክንያት ቀጣይነት ባለው እና በግለሰብ ደረጃ ለመጠቀም በተዘጋጀ ውጤታማ ባልሆነ የሰው ልጅ መሠረተ ልማት ምክንያት ምን ያህል ውሃ እንደሚባክን ማሰብ ይቻላል።

በማኅበረሰቦቻችን ላይ ማሰላሰል እና ቁስሎችን መፈወስ

በኢዮቤልዩ ዓመት ለምድር የሚሰጥ ዕረፍት የሰው ልጅ ማከናወን ካለበት የምርታማነት ሥራ ራሱን ለማሳረፍ መፈለግን ያሳያል። በዓለም ላይ እንዴት እንደምንኖር ለማሰላሰል እና የጋራ እና ሰብዓዊ መፍትሄዎችን ለማግኘት ጊዜ እንድንወስድ የቀረበ ግብዣ ነው። ቅዱሳት መጻሕፍት ከመሬት እና ከምግብ አለመመጣጠን ጋር የተያያዙ ማኅበራዊ ቁስሎችን ለመፈወስ የሚያነሳሱ የጋራ መሣሪያዎችን በጋራ እንድንጠቀማቸው ያሳስቡናል።

የምድርም ሰንበት ለአንተ፥ ለወንድ እና ለሴት ባሪያህም፥ ለምንደኛውም፥ ከአንተ ጋር ለሚኖር ለመጻተኛም ምግብ ይሁን።(ዘሌዋውያን 25:6)። በዕረፍት ላይ የምትገኝ ምድረ በዳ እና ደረቅ ምድር አይደለችም። ነገር ግን ዳግም የምትወለድ እና የምትለውጥ ለም ቦታ ናት።

 

12 Nov 2025, 09:35