ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የቀረበ የሐዘን መግለጫ
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በምንጃር ሸንኮር አረርቲ ደበረ ገነት ቅድስት ማርያም ለቤተ ክርስቲያን ሕንፃ ግንባታ የተሠራ የእንጨት ርብራብ በመደርመሱ ምክንያት የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና በርካቶችም የአካል ጉዳት እንዳጋጠማቸው የሰማነው በታላቅ ሀዘን ነው፡፡
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በዚህ ድንገተኛ አደጋ የተሰማንን ሀዘን እየገለጽን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለይም ለአረርቲ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች፣ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ እና ለተጎዱ ቤተሰቦች ፈጣሪ መጽናናት እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን፡፡
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ
ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት
02 Oct 2025, 11:36