ንግሥት ካሚላ ከዓለም አቀፍ ገዳማዊያት ማህበራት እህቶች የበላይ አለቆች ጋር በተገናኙበት ወቅት ንግሥት ካሚላ ከዓለም አቀፍ ገዳማዊያት ማህበራት እህቶች የበላይ አለቆች ጋር በተገናኙበት ወቅት 

ንግሥት ካሚላ ከዓለም አቀፍ ገዳማዊያት ማህበራት እህቶች የበላይ አለቆች ጋር ተገናኙ።

በእንግሊዜኛው ምጻረ ቃል "UISG" በመባል የሚታወቅ ሲሆን ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የገዳማዊያት ማሕበራት እሁቶች የበላይ ዋና አለቆች ሕብረት የሚወክል ሲሆን በሕጋዊ እና በቀኖናዊ መልኩ ፍቃድ ያለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሴቶች ገድማዊያን ማሕበራት የበላይ ዋና አልቆች ሕብረት የሚወክል ማሕበር ነው።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ንግሥት ካሚላ ከዓለም አቀፉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የግዳማዊያት እህቶች የበላይ አለቆች ሕብረት አባላት (UISG) ከሚወክሉ የካቶሊክ እህቶች ቡድን ጋር ተገናኝተዋል፣ ይህም የገዳማዊያት እህቶች ማሕበር የበላይ አለቆች በቤተክርስቲያንም ሆነ በዓለም ላይ ትንቢታዊ ድምጽ እና ምስክር እንዲሆኑ ያስችላቸዋል ሲሉ አድኖት ሰጥተው ገልጸዋል።

ንግሥት ካሚላ ሐሙስ ዕለት ጥቅምት 13/2018 ዓ.ም በሮም ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የካቶሊክ ገዳማዊያት እህቶች ማሕበር የበላይ አለቆች ሕብረት (UISG) ከተውጣጡ እህቶች ጋር ተገናኝተው በዓለም ዙሪያ በግጭት፣ በድህነት እና በመፈናቀል ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን ለማጀብ ላደረጉት አገልግሎት ያላቸውን ጥልቅ አድናቆት ገልጸዋል።

ይህ ስብሰባ የተካሄደው በቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ ውስጥ ከተካሄደው የጸሎት ሥነ-ሥርዓት በኋላ ሲሆን ንጉሥ ቻርለስ ሳልሳዊ እና ንግሥት ካሚላ በቅድስት መንበር በይፋ ጉብኝታቸውን በምያደጉበት ወቅት እንደነበረም ተገልጿል።  

ንጉሡ ከዐብይ ዘርዓ ክህነት ተማሪዎች አለቃ እና ተማሪዎች ጋር ሲገናኙ፣ ንግሥቲቱ ከስድስት የUISG ተወካዮች ጋር መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን  እነሱም ስለ ሥራቸው እና በአህጉራት ውስጥ ያሉ ገዳማዊያት እህቶች ለሰው ልጅ ክብር በማገልገል የሚያስተሳስረውን ተልዕኮ ታሪክ አጋርተዋል።

በውይይቱ መጨረሻ ላይ እህቶቹ ለንግሥት ካሚላ የፈጠሩትን ምሳሌያዊ ሥዕል ለንግሥት ካሚላ አቅርበዋል፤ የUISG ዓለም አቀፍ የፀረ-ሕገወጥ ዝውውር ኔትወርክ አባል የሆኑት እህት ሳንድራ ደ ፊሊፒስ ሥዕሉ በማዕከሉ ላይ፣ ሊበር የተቃረበ ወፍ ያለው፣ የተዘረጋ እጅ ያላቸው የሴቶችና የህፃናትን የቆሰሉ ሆኖም ግን ጠንካራ ፊት ያሳያል። ይህ ሥዕል መከራንም ሆነ ለውጥን ይወክላል - የታሊታ ኩም ዓለም አቀፍ አስተባባሪ እህት አቢ አቬሊኖ “በጥልቅ ህመም ውስጥም ቢሆን ብርሃን፣ ውበት እና ተስፋ ሊኖር ይችላል” ሲሉ አስረድተዋል።

የዓለም አቀፉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የግዳማዊያት እህቶች የበላይ አለቆች ሕብረት ንግሥት ካሚላ  የሰጡት የሥዕል ስጦታ
የዓለም አቀፉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የግዳማዊያት እህቶች የበላይ አለቆች ሕብረት ንግሥት ካሚላ የሰጡት የሥዕል ስጦታ

ንግሥቲቱ እህቶችን ለስጦታው እና ለታሪኮቻቸው አመስግነዋል። “የምታደርጉትን መስማት እጅግ በጣም ያስደስታል” ብለዋል። “በሥራችሁ እና በምታገለግሏቸው ሰዎች ጥንካሬ እና ድፍረት ከእናንተ ትህትናን ተምርያለሁ" ብለዋል።

ዓለም አቀፍ የገዳማዊያት እህቶች ሕብረት

ሕብረቱን በማስተዋወቅ ዓለም አቀፍ የገዳማዊያት እህቶች የበላይ አለቆች ሕብረት (UISG) ሥራ አስፈፃሚ ጸሐፊ የሆኑት እህት ሮክሳን ሻሬስ የድርጅቱን ተልዕኮ እና ተደራሽነት አብራርተዋል።

“ዓለም አቀፍ የገዳማዊያት እህቶች የበላይ አለቆች ሕብረት (UISG) ከ95 አገሮች የተውጣጡ ከ1,900 በላይ የገዳማዊያት እህቶች ማሕበራትን ያሰባስባል” ብለዋል። “በአንድነት፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ ለማገልገል የሚኖሩ እና የሚያገለግሉ ወደ 600,000 የሚጠጉ እህቶችን እንወክላለን - በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታሎች፣ በስደተኞች ካምፖች፣ በገጠር በሚስዮን እና ብዙውን ጊዜ በዳር ላይ ባሉ የተገለሉ ማህበረሰቦች ውስጥ" መንፈሳዊ እና ማሕበራዊ አገልግሎታችንን እናከናውናለን ብለዋል።

እህት ሮክሳን ማሕበሩን “የኅብረት እና የአንድነት አውታረ መረብ” ሲሉ ገልጸውታል፣ ይህም በትምህርት፣ በጤና አጠባበቅ፣ በማህበራዊ ሥራ፣ በተሟጋችነት እና በሥነ-ምህዳር ፍትህ ላይ የተሰማሩ ገዳማዊያት እህቶችን ያገናኛል ያሉ ሲሆን “እህቶቻችን በገዳማት ውስጥ አልተዘጉም፤ በዓለም ላይ ይገኛሉ - ስደተኞችን፣ ጥገኝነት ጠያቂዎችን፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚፈጸምባቸውን ሰዎች እና ድሆችን በማገልገል ላይ እንገኛለን" ብለዋል።

እህት አቢ አቬሊኖ እና እህት ፓትሪሺያ መሬይ
እህት አቢ አቬሊኖ እና እህት ፓትሪሺያ መሬይ

ስደተኞች የተስፋ ምዕመናን ናቸው

የራሳቸውን የሚስዮናዊነት ልምድ በመጥቀስ፣ እህት ሮክሳን በኬንያ ከኢየሱሳዊያን ማሕበር በሚተዳደረው የስደተኞች አገልግሎት ተቋም ጋር የአስር ዓመታት አገልግሎታቸውን አስታውሰዋል። “የተገናኘኋቸው ስደተኞች በእውነት የተስፋ ምዕመናን ናቸው” ብለዋል። “በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ቤታቸውን ለቀው ለቤተሰቦቻቸው ሕይወት እና ጥበቃ ይፈልጋሉ። ድፍረታቸው እና ጽናታቸው ኃይለኛ ምስክር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የአራት ዓመት ልጅ የሆነችውን የሩዋንዳ ወጣት ልጅ፣ አባታቸውና ወንድማቸው ከጠፉ በኋላ ከአራት ዓመቷ እህቷ ጋር እንደሸሸች ትናገራለች። “ናይሮቢ ደርሰው ለመኖር ታገሉ” ያሉ ሲሆን “የቅርጫት ሽመና ተምራለች፣ ከጊዜ በኋላም ወደ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ተላከች። በኋላ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ተመልሳ ትምህርቷን አጠናቀቀች፣ እና በቅርቡ የመጀመሪያ ልጇን ፎቶ ልካለች። ታሪኳ ተስፋ ምን ሊያሳካ እንደሚችል የሚያሳይ ምልክት ነው” ሲሉ ገጠመኛቸውን አካፍለዋል።

እህት ማማሊፋር ፖሬኩ
እህት ማማሊፋር ፖሬኩ

ተስፋ በተሟጠጠበት ቦታ የሚሰሩ እህቶች

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UISG) ተወካዮች መካከል እህት አቢ ይገኙበታል፣  እርሳቸውም በሰዎች ሕገ ወጥ ዝውውር ላይ  ያላቸውን የአገልግሎት ታሪክን አካፍለዋል። “ከተልዕኮ በላይ ነው፣ የርህራሄ ጥሪ ነው፣ በጣም ልዩ የሆነ እንክብካቤ የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች አሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

“በሰውነት፣ በአእምሮ እና በመንፈስ የተጎዱ ሴቶችን እና ልጆችን ሳገኝ፣ ተልእኳችን ከአሰቃቂ ሁኔታ ወደ ፈውስ እና ነፃነት አጅበን መሄድ እንደሆነ ተረድቻለሁ” ሲሉ የተናገሩ ሲሆን በተስፋ መቁረጥ ጊዜያት እንኳን፣ ደስታን እና እድሳትን እናያለን። በትብብር፣ ትናንሽ ምልክቶች እንኳን ለሕይወት እና ለተስፋ ክፍት መንገዶችን ሊሰጡ ይችላሉ” ብለዋል።

ታሊታ ኩም ("ታሊታ ኩም" የሚለው አገላለጽ "አንቺ ልጅ ተነሺ!" የሚል ትርጉም ያለው የአረማይክ አገላለጽ ነው። ይህ አገላለጽ ኢየሱስ በማርቆስ ወንጌል (5:41) የኢያኢሮስን ልጅ ከሞት ሲያስነሳ የተናገረው ሐረግ ነው። ይህ አገላለጽ የሰዎችን ሕገወጥ ዝውውር ለመዋጋት ቁርጠኛ የሆነ ዓለም አቀፍ ድርጅት የሆነው 'ታሊታ ኩም' ስም ሆኗል) እህቶችና ወጣቶች ግንዛቤን እንዲያሳድጉ፣ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን እንዲከላከሉ እና የተረፉትን እንዲደግፉ የሚያበረታታ ዓለም አቀፍ አውታረ መረብ ሆኖ እንደሚሠራ አብራርተዋል።  “ለግርማዊቷ ያቀረብነው ሥዕል” እህት አቢ አክለውም እንደ ተናገሩት ከሆነ “የዚህ ትብብር ምልክት ነው - በእምነትና በአንድነት አንድ ላይ መከራን ወደ አዲስ ጅምር መለወጥ እንደምንችል የሚያስታውስ ነው” ብለዋል።

በስፍራው ከተገኙ እህቶች መካከል እህት ፓትሪሺያ መሬይ የቀድሞዋ የUISG ሥራ አስፈፃሚ ጸሐፊ፤ እህት ኤስፔራንስ ባሚሪዮ፣ የደቡብ ሱዳን የካቶሊክ የጤና ማሰልጠኛ ተቋም የቀድሞ ዳይሬክተር፤ እህት ሞኒካ ጆሴፍ፣ የኢየሱስ እና የማርያም ማሕበር የበላይ ዋና አለቃ፤ እና እህት ማማሊፋር ፖሬኩ፣ የUISG ሥራ አስፈፃሚ ተባባሪ ጸሐፊ ይገኙበታል።

ሁሉም የመዳን፣ የተዋሃዱ የልማት ፕሮጀክቶችን፣ የትምህርት ተነሳሽነቶችን እና ሴቶችን እና ወጣቶችን ለማብቃት የታለሙ የአካባቢ ጥረቶችን ታሪኮች አጋርተዋል። በባለጠጎች እና በድሆች መካከል ያለው ልዩነት እያደገ በመምጣቱ ዓለም በጦርነት መበታተኗ እንዲቀጥል አድርጓል፣ ነገር ግን ሁሉም ሙያቸው ሕይወት በጣም ደካማ በሆነችበት ቦታ ተስፋን ለማምጣት እንደሚጠራቸው አረጋግጠዋል።

ንግሥት ካሚላ እህት አቢን ስያዳምጡ
ንግሥት ካሚላ እህት አቢን ስያዳምጡ

ንግሥት ካሚላ “በሥራችሁ ትህትና" ተማርክያለሁ

ንግሥት ካሚላ እያንዳንዱን ምስክርነት በትኩረት ከአዳመጡ በኋላ ለእህቶች ቁርጠኝነት ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። “በዓለም ዙሪያ ይህን ሥራ የሚሠሩ ብዙ እህቶች እንዳሉ አላወቅኩም ነበር” ብለዋል። “አስደናቂ እና ጥልቅ ትህትና የተሞላበት ተግባር ነው” ብለዋል።

ንግሥቲቱ “በጨለማ ቦታዎች ብርሃን የሚያመጣ ሥራ” ብለው ተግባራቸውን የገለጹ ሲሆን እናም ለዘላቂ የእምነት እና የርህራሄ ምስክርነታቸው የUISG አባላትን አመስግነዋል።

እህቶቹ በኋላ ላይ ስብሰባው ቀለል ባለ ሁኔታ፣ በቅንነት እና በጋራ አክብሮት የተሞላበት እንደነበር ተናግረዋል። “ንግሥቲቱ በታሪኮቹ በጣም ተነክተዋል” ሲሉ ስለስብሰባው የገለጹት እህት ሮክሳን “እኛም በተራው እርሳቸው በሰጡት ትኩረት እና ተልዕኳችንን ለመረዳት በነበራቸው ፍላጎት ተነክተናል” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

እህት ኢስፔራንስ ባሚሪዮ እና እህት ሞኒካ ጆሴፍ
እህት ኢስፔራንስ ባሚሪዮ እና እህት ሞኒካ ጆሴፍ

“የእግዚአብሔር መንፈስ መጋራት”

ከስብሰባው በኋላ እህት ሮክሳን የስብሰባውን እና የልምድ ልውውጡን አስፈላጊነት ለቫቲካን ኒውስ ሲናገሩ  “እንደዚህ ያሉ ጊዜያት ቆም ብለን በተልዕኮአችን ላይ እንድናሰላስል ይጋብዙናል - የእግዚአብሔር መንፈስ ወዴት እየመራን እንደሆነ ለማየት፣ እንደ ንግሥቲቱ ያሉ ሰዎች ፍላጎት እና አሳቢነት ሲያሳዩ፣ በአዲስ ጉልበት እንድንቀጥል ያበረታታናል” ሲሉ አስረድተዋል።

ስብሰባውን “እየተጓዝን እንድንሄድ የሚያደርገን የእግዚአብሔር መንፈስ መጋራት” ሲሉ የእህቶች ሥራ በመገኘት እና በማጀብ ላይ የተመሠረተ መሆኑን አክለው የገለጹ ሲሆን “ብዙዎች በትህትናና እና በጸሎት የሚኖሩ ናቸው” ብለዋል፣ “ሌሎች ደግሞ በግንባር ቀደምትነት - በትምህርት፣ በጤና አጠባበቅ፣ በሰላም ግንባታ እና በሐዋርያዊ እንክብካቤ አገልግሎት ላይ ያገለግላሉ” ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

እህት ሮክሳን በስደተኞች መካከል ያጋጠሟቸውን ተሞክሮ እንደገና በማስታወስ፣ እህት ሮክሳን እንደ ተናገሩት ለ25 ዓመታት የተፈናቀለውን ሰው ታሪክ ተናግረዋል። “ምን እንዳስቻለው ጠየቅኩት፣ ለክርስቲያን፣ ሁልጊዜ ተስፋ አለ። እግዚአብሔር መቼ ወደ ቤት መመለስ እንደምችል ያውቃል፣ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ፣ ዘጠነኛ ልጁ ተወለደች -- ሚስቱ ልጇን እግዚአብሔር ያውቃል ብላ ሰየመችው” ሲሉ የገጠማቸውን ሁኔታ አካፍለዋል።

“እምነትና ጽናት ነው” ያሉት እህት ሮክሳን “ተልእኳችንንና ተስፋችንን ማነሳሳቱን የቀጠለው እምነት ነው” ካሉ በኋላ ንግግራቸውን ደምድመዋል።

ንግሥት ካሚላ ከዓለም አቀፉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የግዳማዊያት እህቶች የበላይ አለቆች ሕብረት አባላት
ንግሥት ካሚላ ከዓለም አቀፉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የግዳማዊያት እህቶች የበላይ አለቆች ሕብረት አባላት

 

24 Oct 2025, 15:27