የቅዱስ አጎስጢኖስ ማኅበር እሴቶች፥ እውነት፣ አንድነት እና ፍቅር መሆናቸው ተገለጸ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
በቪላኖቫው ቅዱስ ቶማስ የአጎስጢናውያን ማኅበር አውራጃ ጠቅላይ አለቃ አባ ሮበርት ሃጋን፥ “በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የቀድሞው ስማቸው ሮበርት ፕሬቮስት የሚከበረው የቅዱስ ሮበርት ቤላርሚን በዓል፥ “የቅዱስ አጎስጢኖስ ማኅበር ገዳም ወንድማቸው ለቅዱስ ጴጥሮስ መንበር መመረጣቸው ዓለም የቅዱስ አጎስጢኖስን እሴቶች ማለትም ‘እውነትን፣ አንድነትን እና ፍቅርን እንደገና እንዲያውቅ ዕድል የሚሰጥ እንደሆነ ያምናሉ” ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛን ለ27 ዓመታት የሚያውቋቸው አባ ሃጋን፥ ከእግዚአብሔር ጋር ካላቸው ጥልቅ የጸሎት ግንኙነት እና ከሰዎች ጋርም የመቀራረብ ፍላጎት እንዳላቸው አበክረው ገልጸዋል።
አባ ሮበርት ሃጋን፥ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ከእግዚአብሔር ጋር ጥልቅ የጸሎት ግንኙነት እና ከሰዎች ጋር የመሆን ፍቅራዊ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው፥ “እኚሁ የቅዱስ አጎስስጢኖስ ልጅ አሁን ለሁላችንም መልካም እረኛ ናቸው” ብለዋል።
በወቅቱ አባ ሮበርት ፍራንሲስ ፕሬቮስት ተብለው የሚጠሩት፥ በቺካጎ በነበሩበት ወቅት የማኅበሩ የአውራጃው ጠቅላይ አለቃ በኋላም የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ ሆነው ማገልገላቸውን የሚያስታውሱት አባ ሮበርት ሃጋን፥ “መሐላዬን የገባሁት በወቅቱ የማኅበሩ ጠቅላይ አለቃ በነበሩት በአባ ሮበርት ፕሬቮስት ፊት ነው” ስሉ አስታውሰው፥ “ደግና ሰውን በቀላሉ የሚቀርቡ እንደ ሆኑ፥ በዚህ ሚናቸው እግዚአብሔር የሁላችን መሪ አድርገው እንደመረጣቸው እናውቃለን” ብለዋል።
የቅዱስ አጎስጢኖስ ማኅበርተኞች መሠረቶች
አባ ሮበርት ሃጋን፥ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ መንፈሳዊነት በቅዱስ አጎስጢኖስ እሴቶች ላይ ሥር የሰደደ እና ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ማለት በሰዎች መካከል የመገናኛ ድልድይን የሚገነባ ማለት ነው” ሲሉ አስረድተው፥ የእርሳቸው ቃላት የቅዱስ አጎስጢኖስ ማኅበር የሰላም፣ የወዳጅነት እና የማኅበር ጥሪን የሚያስተጋቡ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል።
“ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ዓለም ዛሬ እጅግ የሚፈልገውን እውነት፣ አንድነት፣ ፍቅር እና ወዳጅነት እንዲያገኝ የሚረዱ ናቸው” ብለዋል።
አባ ሮበርት ሃጋን፥ “አዲሱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በተግባቦት ዘይቤያቸው የተረጋጉ፣ ግልጽ እና ለሁሉም ደራሽ በመሆን የምእመናንን ድጋፍ አግኝተዋል” ብለዋል። “ሰዎች በሙሉ ወጣቶችም እንደ እርሳቸው የዚህ መንፈስ ተካፋይ እንዲሆኑ መጋበዛቸውን ገልጸው፥ ሌሎችም ጭምር ተመልሰው እንዲመጡ ግብዣ እየቀረበላቸው ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
የተልዕኮ እና የማኅበረሰብ ሰው
“የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ዳራ አስፈላጊ አካል የሚስዮናዊነት ሥራቸው ነው” ያሉት አባ ሮበርት ሃጋን፥ በውልደት አሜሪካዊ ቢሆኑም ነገር ግን በፔሩ ለ20 ዓመታት ያህል ድሆችን ማገልገላቸውን አስታውሰው፥ የተማሩት ቋንቋቸውን ብቻ ሳይሆን ባሕላቸውንም ጭምር እንደሆነ አስረድተዋል።
“በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ሠገነት ላይ የቆመው ማነው? ወንድማች ነው!”
አባ ሮበርት ሃጋን፥ በአዲሱ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ምርጫው ቀን የተሰማቸውን ስሜት በማስታወስ ሲናገሩ፥ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ሠገነት ላይ የቆመው ወድንማቸው ካርዲናል ሮቤርር ፍራንችስኮ ፕሬቮስት መሆናቸውን የቪላኖቫ ግዛት ሰዎች በለቅሶ፣ በሳቅ እና በመተቃቀፍ ደስታቸውን ይገልጹ እንደ ነበር አስታውሰው፥ ተማሪዎችም በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት አብረዋቸው በአንድ ክፍል ውስጥ የተማሩት እና በአንድ ምግብ ቤት የተመገቡት ዛሬ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነዋል” ሲሉ ማስታወሳቸውን ተናግረው፥ በማከልም፥ “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በመጀመሪያዎቹ የሐዋርያዊ ስልጣን ወራት፣ የሰላም እና የዕርቅ መልዕክት አስተላልፈዋል” ብለዋል።
የቅዱስ አጎስጢኖስ ማኅበር ገዳማውያን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ናቸው!
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን ለማካሄድ ወደ ሮም ለመጡ የቅዱስ አጎስጢኖስ ማኅበር ገዳማውያን እና ገዳማዊያት መስከረም 5/2018 ዓ. ም. ባስተላለፉት መልዕክት፥ “የማኅበር ሕይወታችንን እና ሐዋርያዊ ተግባራችንን በተሟላ ሁኔታ ለመምራት ከፈለግን ቁሳዊ ንብረቶቻችንን፣ ሰብዓዊ እና መንፈሳዊ ጥረቶቻችንን ለመጋራት ከፈለግን ልንመለከተው የሚገባን መለኮታዊ የበጎነት ስጦታን ነው” ብለዋል። “በወንድማማችነት ደስታ፣ ልባችሁ የመንፈስ ቅዱስን ጥቆማዎች እንዲቀበል በማዘጋጀት፣ የእግዚአብሔር የበጎነት ሃሳባችሁን እና ተግባራችሁን በማነሳሳት ሐዋርያት እና በዓለም የወንጌል ምስክሮች በማድረግ የማኅበሩን ጠቅላላ ምዕራፍ ጉባኤን ልትቀጥሉ ይገባል” ሲሉ አሳስበዋል።