ፈልግ

በቅዱስ ኤጅዲዮ ማህበረሰብ በሮም የተዘጋጀው "ሰላም ለጋዛ" የተሰኘው የፀሎት መርሃ ግብር በቅዱስ ኤጅዲዮ ማህበረሰብ በሮም የተዘጋጀው "ሰላም ለጋዛ" የተሰኘው የፀሎት መርሃ ግብር  

‘ሰላም ለጋዛ’ የተሰኘ የፀሎት መርሃ ግብር መዘጋጀቱ ተነገረ

የቅዱስ ኤጂዲዮ ማህበረሰብ ከበርካታ የካቶሊክ ማህበራት እና ንቅናቄዎች ጋር በመሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛው ላቀረቡት ጥሪ ምላሽ ይሆን ዘንድ፥ ብሎም በጋዛ ውስጥ ያለው ጦርነት እና የሰብአዊ ሁኔታ አስከፊነትን ለማሳሰብ “ሰላም ለጋዛ” በሚል መሪ ቃል የጸሎት መርሃ ግብር ማዘጋጀቱ ተነግሯል።

አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በዚህ የጸሎት መርሃ ግብር ላይ ሁሉም መልካም ፈቃድ ያላቸው ወንዶች እና ሴቶች ካሉበት ሥፍራ ሆነው እንዲሳተፉ የተጋበዙ ሲሆን፥ የሮም ከተማ ነዋሪዎች ሰኞ ምሽት ላይ፣ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም. በሮም ሰዓት አቆጣጠር በ 7፡30 ጀምሮ ትራስቴቬሬ አከባቢ በሚገኘው ፒያሳ ሳንታ ማሪያ አደባባይ ላይ በተካሄደው መርሃ ግብር ላይ በአካል ተገኝተው እንደተሳተፉ ተገልጿል።

ይህ የጸሎት መርሃ ግብር በብፁዕ ካርዲናል ጓልቲሮ ባሴቲ እና መርሃ ግብሩን በበይነ መረብ አማካይነት ከተቀላቀሉት በኢየሩሳሌም የላቲን ሥርዓተ አምልኮ የምትከተል ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒየርባቲስታ ፒዛባላ እንደተመራም ጭምር ተገልጿል።

የጸሎት እንቅስቃሴው የተዘጋጀው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ “የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲደረግ፣ በሃማስ የተያዙት ታጋቾች እንዲለቀቁ እና በዲፕሎማሲያዊ ድርድር መፍትሔ እንዲመጣ እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ ሕግ ሙሉ በሙሉ እንዲከበር” ላቀረቡት ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ታስቦ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

ይህ ተነሳሽነት እንደ ‘አዚዮኔ ካቶሊካ ኢታሊያና’፣ ህብረት እና ነፃነት፣ የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዮሃንስ 23ኛ ማህበረሰብ፣ የክርስቲያን ሠራተኞች ንቅናቄ፣ የፎኮላሬ እንቅስቃሴ፣ የፖለቲካ ንቅናቄ ለአንድነት፣ ማህበራዊ የፍራንቺስካዊያን ገዳም፣ በመንፈስ ቅዱስ መታደስ እና የበላይ አለቆች ህብረትን የመሳሰሉ በርካታ የካቶሊክ ማህበራትን እና ማህበረሰቦችን አንድ ላይ ያገናኛል ተብሏል።

የጸሎት መርሃ ግብሩ ሰላም እንዲሰፍን፣ የሰው ህይወት እንዲጠበቅ እና ግጭት እንዲቆም የተባበረ ድምጽ ለማሰማት ታልሞ የተዘጋጀ እንደሆነ፥ ምዕመናን እና በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በሙሉ እንዲሳተፉ የተጋበዙ ሲሆን፥ በአካል መገኘት ለማይችሉ በዩቲዩብ ቀጥሎ ባለው ማስፈንጠሪያ አማካይነት በቀጥታ መከታተል እንደሚቻል ተገልጿል።
streamed live on YouTube

23 Sep 2025, 16:12