የዛምቢያ ወጣቶች በሊዝበን በተከበረው የዓለም ወጣቶች ቀን ክብረ በዓል ላይ የዛምቢያ ወጣቶች በሊዝበን በተከበረው የዓለም ወጣቶች ቀን ክብረ በዓል ላይ 

አባ ክሪስቶፈር ኩንዳ፥ ሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን የጋራ መሆኗን አስገነዘቡ

በዛምቢያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ የብሔራዊ ወጣቶች ማኅበር አስተባባሪ አባ ክሪስቶፈር ኩንዳ፥ ወጣቶች የሲኖዶስዊነት ፈለግ ተከትለው በሙሉ አባልነት የስብከተ ወንጌል ተልዕኮአቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ወጣቶች በሲኖዶሳዊነት መንፈስ በቤተ ክርስቲያን የወንጌል ተልዕኮ እና አገልግሎት ንቁ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ያላቸውን ተስፋ፥ በዛምቢያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ (ZCCB) የብሔራዊ ወጣቶች ማኅበር አስተባባሪ አባ ክሪስቶፈር ኩንዳ ገልጸዋል።

በዛምቢያ የዶን ቦስኮ ወጣቶች አስተባባሪ ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አባ ክሪስቶፈር ኩንዳ፥ ሲኖዶሳዊነት በወጣቶች ሕይወት ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችል ከቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስረድተዋል።

ሲኖዶሳዊነት እና ውይይትን ከወጣቶች ጋር ተግባራዊ ማድረግ
አባ ኩንዳ በቫቲካን ሲካሄድ የቆየው የሲኖዶሳዊነት ጉባኤ ቢጠናቀቅም የተጀመሩት ተነሳሽነቶች እና አዳዲስ አቀራረቦች ወጣቶችን በቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች እና አገልግሎቶች ውስት እንዲሰማሩ ማበረታታቱን እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

እንደ ስደተኞች ብዙ ዕድል ለሌላቸው፣ በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙትን ወይም በአስቸጋሪ የግል ሁኔታዎች ውስጥ ለሚገኙት ወጣቶች ምክራቸውን የለገሱት

አባ ኩንዳ፥ እንደ ሳሌዢያ ማኅበር አባልነት ከወጣቶች ጋር እየሠሩ በሲኖዶሳዊነት መንፈስ ለወጣቶች ቅድሚያን እንደሚሰጡ እና በቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ እና አገልግሎት ንቁ ተሳታፊዎች እንደሚሆኑ ያላቸው ተስፋ ገልጸው፥ ወጣቶች ለእኩዮቻቸው በመመስከር እና በማገልገል ወንጌል በዓለም ዙሪያ እንዲዳረስ ማድረግ ይችላሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

ሲኖዶሳዊነትን መተግበር የወጣቶች ተግዳሮት ነው
እንደ ሀገር አቀፍ የወጣቶች አስተባባሪነት፥ ሲኖዶሳዊነት ማለት ቤተ ክርስቲያን በአንድ አቅጣጫ ብቻ የማትናገር መሆኗን ማወቅ መልካም ነው” ያሉት አባ ኩንዳ፥ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በመወጣት ድርሻቸውን ሊወጡ እንደሚገባ፥ በሕይወታቸው እና በአኗኗራቸው ራሳቸውን እና ሌሎችን የመንከባከብ ኃላፊነት አለባቸው” ሲሉ ተናግረዋል።

“በጋራ ኃላፊነት ከሌሎች ወጣቶች ጋር በመሆን ከፍተኛ እንቅስቃሴን መፍጠር የምንችለው፥ ዕድል ያላገኙትን በመንከባከብ እና ለጋራ መኖሪያ ምድራችን በማሰብ ነው” ብለው፥ “በሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁሉም ሰው ቤተ ክርስቲያን ማን እንደሆነች እና ምን መሆን እንዳለባት፣ ይህ ማለት ሁላችን በአንድነት ምን ዓይነት የክርስቲያን ማኅበረሰብን ለመገንባት ሃላፊነት እንዳለብን የሚያሳስብ መሆኑን ተናግረዋል።

ነገር ግን ይህን ሳይገነዘብ የትኛውም የክርስቲያን እንቅስቃሴ የቤተ ክርስቲያን ባለቤት ሊሆን እንደማይችል እና መብትም እንደሌለው አስረድተው፥ በዚህ ሂደት ውስጥ እያንዳንዱ አባል አስፈላጊ እና ሚናውም ከሌላው የተለየ መሆኑን ሲኖዶሱ እንደሚያሳስብ አባ ኩንዳ ገልጸዋል።

አባ ክሪስቶፈር ኩንዳ፥
አባ ክሪስቶፈር ኩንዳ፥

በወጣቶች አገልግሎት ውስጥ የትብብር አገልግሎት
ከዛምቢያ ወጣቶች ጋር ባላቸው ግንኙነት ለትብብር እና ለኃላፊነት ጥሪ አፅንዖት የሰጡት አባ ኩንዳ፥ “የወጣቶች የጋራ አገልግሎት ማለት ተልዕኮው የጋራ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ሰዎችን ወደ መርከቡ የማምጣት ሂደት ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

አባ ኩንዳ ወጣቶች በሕይወት ጉዟቸው ውስጥ ድጋፍ ሊሰጣቸው እንደሚገባ አፅንዖት ሰጥተው፥ የሲኖዶሱ ትክክለኛው ሂደት ወጣቶችን በእምነታቸው፣ በፍርሃታቸው፣ በህልማቸው እና በጭንቀታቸው መደገፍ መሆኑን አስረድተዋል።

ሲኖዶሳዊነት የመተባበር ጽንሰ-ሀሳቦችን በማቅረብ፥ ዕድሎችን የተነፈጉ አንዳንድ ወጣቶችን የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመው፥ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት በሁሉም ደረጃዎች በመሳተፍ በሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አዲስ የወጣትነት መንገዶችን መማር አለባቸው” ሲሉ ተናግረዋል።

አባ ኩንዳ በማጠቃለያቸው፥ ወጣቶች ሲኖዶሳዊነትን እንደ ቤተ ክርስቲያን እና እንደ ሕይወት የአኗኗር ዘይቤ እንዲቀበሉት በማሳሰብ፥ “ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሌሎችን የምታደምጥ ቤተ ክርስቲያን መሆኗን አሳይተውናል” ሲሉ ተናግረዋል።

“ወጣቶች የመደማመጥ እና የውይይት ባሕልን እንዲያሳድጉ ተጠርተዋል” ያሉት አባ ኩንዳ፥ ንቁ ተሳታፊዎች እንጂ ከዳር ቆመው መመለከት እንደማይችሉ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን እስኪጋበዙ ድረስ መጠበቅ እንደሌለባቸው፥ በልቧ ሁሉን አቀፋ የያዘች እውነተኛ ሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን የወጣቶች የፈጠራ ችሎታ ያስፈልጋታል” ሲሉ አስረድተዋል።

 

09 January 2025, 16:11